በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካቴድራል የምግባረ ሰናይ ኮሚቴ እና የሃይማኖተ አበው መዘምራን በጥምር የሚያዘጋጁት የኮቪድ 19 የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር አምስተኛው ዙር በእግዚአብሔር ፈቃድ በግሩም ሁኔታ ተጠናቀቀ። ባለፈው እንደዘገብነው ይህ መርሃ ግብር የተጀመረው 12 በቤተክርስቲያናችን አካባቢ የሚኖሩ ወገኖቻችንን ታሳቢ በማድረግ ነበር። በሦስተኛውና በአራተኛው ዙር፥ ማለትም በሆሳእና እና በትንሣዔ ግን ቁጥሩ አድጎ ለ40 ሰዎች ተደራሽ ሆነናል። እሁድ May 3, 2019 ዙር አምስት አባታችን መላእከ ጽዮን አባ ላዕከማርያም በተገኙበት በሚያስደስት ሁኔታ ተገባዷል። በዚህ በዙር 5 ከፍ ብሎ ለ50 ቤተሰቦች ተደራሽ ሆነናል። በእግዚአብሔር ፈቃድ ኮሮና ከምድረ ገጽ ካልጠፋ ይህ በጎ ተግባር ለዚሁ ጉዳይ በተቋቋመው ግብረ ሃይል ለወገን ተደራሽነቱን ይቀጥላል።

እነኝህ በምስሉ የምትመለከቷቸው ለቤትና ለግለሰብ ጽዳት የሚውሉ ቁሳቁሶች በዙር 5 ለወገኖቻችን የተላኩ ናቸው።

ይህን ተግባር እንድናከናውን ለፈቀደልን ለልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው።

© 2016 Virgin Mary Ethiopian Orthodox Tewahedo Cathedral
Top
Follow us: